Fana: At a Speed of Life!

በቻይና 27 አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተገኙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና 27 አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን አስታወቀች።

የሃገሪቱ ብሄራዊ የጤና ኮሚሽን እንዳስታወቀው ትናንት በቫይረሱ የተያዙ 27 አዲስ ሰዎች በቻይና ተገኝተዋል።

ከዚህ ውስጥ 22ቱ በመዲናዋ ቤጂንግ እንደተገኙም ኮሚሽኑ ገልጿል።

ከዚህ ባለፈም ቫይረሱ ኖሮባቸው ምልክት የማያሳዩ ሌሎች 7 ሰዎች ተገኝተዋልም ነው የተባለው።

ከትናንት በስቲያ በሃገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው አዳዲስ 32 ሰዎች የተገኙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 25ቱ የቤጂንግ ነዋሪዎች ነበሩ።

የሃገሪቱ ባለስልጣናትም አሁን ላይ ዳግም የተቀሰቀሰውን የቫይረሱን ወረርሽኝ ለመግታት የተለያዩ ጥረቶችን እያደረጉ ይገኛል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በተለይም በቤጂንግ የሚገኘውና ቫይረሱ ዳግም እንዲሰራጭ መነሻ ሆኗል በተባለው የመገበያያ ስፍራ አካባቢ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ ሬውተርስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.