የዓለም ጤና ድርጅት በአንድ ቀን ከፍተኛ መጠን ያለው በኮቪድ19 የተያዙ ሰዎች መመዝገቡን አስታወቀ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት ዓለም ላይ በአንድ ቀን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መመዝገቡን አስታወቀ።
ድርጅቱ ዓለም ላይ በአንድ ቀን ከ183 ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ብሏል።
ከዚህ ውስጥ ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑት ብራዚላውያን መሆናቸውንም አስታውቋል።
በተጨማሪም በአሜሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋልም ነው ያለው።
በሌላ በኩል በህንድ ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች 410 ሺህ 461 መድረሳቸው ታውቋል።
ከዚህ ውስጥ ከ15 ሺህ የሚበልጡት ባለፉት 24 ሰአታት ቫይረሱ የተገኘባቸው ናቸው ተብሏል።
ኒው ደልሂ እና ሙምባይ ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ የተሰራጨባቸው ከተሞች መሆናቸውን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል።
በሃገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ 13 ሺህ 254 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።
ምንጭ፡- ቢቢሲ