Fana: At a Speed of Life!

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ነው – ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሃና አርአያስላሴ÷ የተፈጠረው ምቹ መሰረተ ልማት ኢትዮጵያን በቀጣናው ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ አድርጓታል ብለዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ትግበራው ደግሞ ለኢንቨስትመንት ልማት ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እየጨመረ ቢመጣም ኢንቨስተሮች ትርፋቸውን በውጭ ምንዛሬ መውሰድ አለመቻላቸው ለዘርፉ ማነቆ ሆኖ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም መንግስት ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ እድገት በማስመዝገብ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ ተገብቷል ብለዋል፡፡

የፖሊሲ ማሻሻያው የዘርፉ ፈተናዎችን በመፍታት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰቱን በማሳደግ ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባት እንደሚያስችል ጠቁመዋል፡፡

በዘርፉ የተሰማሩ ኢንቨስተሮችን ጥያቄዎች የሚመልስ፤ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱን በዘላቂነት የሚፈታ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.