የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ራሳቸውን አገለሉ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማክኪ ሳል በኮሮና ቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር መገናኘታቸውን ተከትሎ ራሳቸውን አግልለዋል።
ፕሬዝዳንቱ በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮና ቫይረስ ባይገኝባቸውም ለጥንቃቄ ሲባል ለሁለት ሳምንታት ያህል ራሳቸውን አግልለው እንደሚቀመጡ ከፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት በተሰጠው መግለጫ ተገልጿል፡፡
የሴኔጋል የሕግ ባለሙያ የያ ዲያሎ በትናንትናው ዕለት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አስታውቀዋል ፡፡
ባለሙያዋ ሰዎች የግል ንፅህናን ከመጠበቅ ባለፈ ማህበራዊ ፈቀቅታን እና የመሳሰሉትን አስፈላጊ የግል እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
በሴኔጋል እስካሁን በኮቪድ 19 ወረርሽኝ 6 ሺህ 129 ሰዎች የተያዙ ሲሆን፥ 93 የሚሆኑት ደግሞ በቫይረሱ ህወታቸው ማለፉ ተነግሯል።
ምንጭ፦ቢቢሲ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።