Fana: At a Speed of Life!

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የልማት ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በካማሽ ዞን ሰዳል ወረዳ የሌማት ትሩፋት እና ሌሎች የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ከግብርና ሚኒስትሩ በተጨማሪ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ጌታሁን አብዲሳ፣ የግብርና ቢሮ ኃላፊ ባበክር ኸሊፋ እና የዞን የሥራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

በዞኑ የአባይን ወንዝ ተከትሎ የተቀመጠው የሰዳል ወረዳ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የተደራጁ አምስት ማህበራት በቀን ሰባት ኩንታል አሣ ለገበያ በማቅረብ ከ80 ሺህ ብር በላይ ገቢ እያገኙ መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.