Fana: At a Speed of Life!

በዓለም በዕድሜ ትልቋ አዛውንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም በዕድሜ ትልቋ የሆኑት ጃፓናዊቷ ቶሚኮ ኢቶካ በ116 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ቶሚኮ ኢቶካ ስፔናዊቷ ብራንያስ ሞሬራ በፈረንጆቹ ነሐሴ 2024 በ117 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ ነበር በዓለም ትልቋ የዕድሜ ባለጸጋ መሆን የቻሉት፡፡

በፈረንጆቹ መስከረም 2024 ላይም ቶሚኮ ኢቶካ በዓለም በዕድሜ ትልቋ አዛውንት በሚል በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ስማቸው ሰፍሯል፡፡

እማማ ቶሚኮ ኢቶካ የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ከመከሰቱ 6 ዓመታት በፊት ወይም ፎርድ ሞዴል መኪና ይፋ በሆነበት በፈረንጆቹ 1908 መወለዳቸውን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል፡፡

ጃፓን 124 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ያላት ሲሆን÷አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት ከ65 ዓመት በላይ ዕድሜ እንዳስቆጠሩ ተነግሯል፡፡

በ16 ቀን ብቻ ከቶሚኮ ኢቶካ የሚያንሰው ብራዚላዊው ኑን ኢናህ ካናባሮ ሉካስ ቀጣዩ የዓለማችን በዕድሜ ትልቁ አዛውንት በመባል በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ እንደሚሰፍር ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.