Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 2ኛው ዙር ዕጩ የሠላም ሠራዊት አባላት ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 ዓ.ም 2ኛው ዙር ዕጩ የሠላም ሠራዊት አባላትን አስመርቋል፡፡

የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ተመራቂዎች መቀራረብን፣ በጋራ አጀንዳ ላይ መግባባትንና የሕዝቦችን ትስስር በመፍጠር አንድነትና ወንድማማችነትን ማጠናከር ላይ ይሰራሉ፡፡

ተመራቂዎች በቀጣይ የጸጥታ አጠባበቅ ሥራ ላይ የሚሰጣቸውን ሃላፊነት በተገቢው ሁኔታ እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በበኩላቸው÷ ተመራቂዎች መጪው የጥምቀት በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር ከጸጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡

የሰላም ሰራዊቱ በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን የመጠበቅ ሃላፊነት እንዳለባቸው ማስገንዘባቸውንም የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.