Fana: At a Speed of Life!

በቦሮና ዞን ከአንድ ላም ሆድ ውስጥ 50 ኪ.ግ የሚመዝን ፕላስቲክ ተወገደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ቦሮና ዞን ስድስት አባላት ያሉት የእንስሳት ሀኪም ቡድን 50 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፕላስቲክ ከአንድ ላም ሆድ በቀዶ ህክምና ማስወገዳቸው ተነግሯል።
 
ቢቢሲ እንደዘገበው ባለሙያዎቹ ሶስት ሰዓት በፈጀው የቀዶ ህክምና ከላሟ ሆድ ውስጥ የነበረውን ፕላስቲክ አስወግደዋል።
 
ዶክተር ፍራኦል ዋቆ የተባሉት የህክምና ቡድኑ አባል ላሟ በአሁኑ ወቅት በህይወት እንዳለችና ጤናማ መሆኗን ገልፀዋል።
 
ላሞቹ በግጦሽ መሬት ወይም በማዕድናት አጥረት እንዲሁም ፕላስቲኮች በሚወገዱበት መንገድ ምከንያት እንስሳቶቹ ፕላስቲኮቹን ሊመገቡ እንደሚችሉና ይህም ለእንስሳቶች ጤና ችግር መሆኑን ዶክተሩ ተናግረዋል።
 
አሬሪ ጨሪ የተባሉት የላሟ ባለቤት ከአንድ ወር በፊት አንድ ላም አምጥተው 20 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፕላስቲክ በባለሙያዎቹ እደተወገደ ዘገባው አመልክቷል።
 
ዶክተር ፍራኦል ከዚህ ቀደም ድጋፍ ስላደረግንለት አምኖናል ሲል የላሟ ባለቤት ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እነሱ የመጣበትን ምክንያት ተናግሯል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.