Fana: At a Speed of Life!

በግማሽ ዓመት ከ2 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ መገዛቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሥድስት ወራት በሀገር ውስጥ ለሽያጭ የሚውል 2 ሚሊየን 41 ሺህ 135 ነጥብ 332 ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ግዥ መፈጸሙ ተገለጸ፡፡

ለመግዛት ታቅዶ የነበረው 2 ሚሊየን 216 ሺህ 189 ሜትሪክ ቶን መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር በቀለች ኩማ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ቤንዚን 313 ሺህ 3፣ ነጭ ናፍጣ 1 ሚሊየን 283 ሺህ 801፣ የአውሮፕላን ነዳጂ 403 ሺህ 17፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 13 ሺህ 390 እና ከባድ ጥቁር ናፍጣ 26 ሺህ 925 ሜትሪክ ቶን ግዥ መፈጸሙን አብራርተዋል፡፡

የዕቅዱን 92 በመቶ መፈጸም መቻሉን ጠቁመው÷ አፈጻጸሙ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ1 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ጠቅሰዋል፡፡

በሌላ በኩል በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ 2 ሚሊየን 112 ሺህ 602 ሜትሪክ ቶን የተጣራ ነዳጅ ምርቶች ለመሸጥ ታቅዶ 2 ሚሊየን 48 ሺህ 687 ሜትሪክ ቶን ነዳጅ መሸጡን እና አፈጻጸሙም 97 በመቶ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የነዳጅ ሽያጭ ክንውን አፈጻጸም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ7 በመቶ ጭማሪ አለው ብለዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.