በድንገተኛ ፍተሻ 18 ኩንታል አደንዛዥ ዕጽ ተያዘ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ ፖሊስ በሻሸመኔ መግቢያ በኩል ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 18 ኩንታል አደንዛዥ ዕጽ መያዙን አስታወቀ፡፡
አደንዛዥ ዕጹ በደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ተጭኖ ሲንቀሳቀስ ከሁለት ግለሰቦች ጋር እጅ ከፍንጅ መያዙን የከተማዋ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡