ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በአጋሮ እና በሻሻ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥር18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በአጋሮ እና በሻሻ የተለያዩ የልማት ሥራዎች ጎብኝተዋል፡፡
ከተጎበኙት የልማት ሥራዎች መካከልም÷ የመንገድ፣ ሻይ ቅጠል ልማት እና ችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች ይገኙበታል፡፡
በተጨማሪም ትምህርት ቤት፣ የአጋሮ ኮሪደር ሥራ እና የአቮካዶ ዘይት መጭመቂያ የጉብኝቱ መዳረሻ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡