Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ብሪታንያ የ4 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያና ብሪታንያ የ4 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር (105 ሚሊየን ፓውንድ) ሁለት የድጋፍ ስምምነቶችን  ተፈራረሙ።

የድጋፍ ስምምነቱንም የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና የብሪታንያ የአፍሪካ ሚኒስትር ጀምስ ደድሪጅ  ናቸው በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተፈራረሙት።

በዚህም መሰረት የመጀመሪያው የድጋፍ ስመምነት በ60 ሚሊየን ፓውድ የሚተገበር ሲሆን፥ ድጋፉም ለመሬት ኢንቨስትመንት ትራንፎርሜሽን ትግበራ የሚውል እና በአራት ክልሎች ማለትም (በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ እና ደቡብ ክልል) የሚተገበር መሆኑም ታውቋል።

በዚህምለ 7 ሚሊየን የመሬት ይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ የሚሰጥ ሲሆን፥ ሁለተኛ ዙር የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ በሚሰጥባቸው 103 ወረዳዎችንም ኮምፒውተራይዝድ የማድረግ ስራ ይተገበራል።

የገንዘብ ድጋፉም የ1 ነጥብ 2 ሚሊየን አነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ አርሶ አደሮችን ገቢ በ15 በመቶ እንደሚያሳድግም ነው የሚጠበቀው።

ሁለተኛው የድጋፍ ስምምነት ደግሞ የ45 ሚሊየን ፓውንድ ሲሆን፥ ይህም የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ለማጠናከር የሚውል መሆኑም ታውቋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.