ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ዳሬ ሰላም ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ገብተዋል።
አቶ ተመስገን ወደ ዳሬ ሰላም ያቀኑት ለ3ኛ ጊዜ በሚካሔደው የጂ-25 የአፍሪካ ቡና አምራች ሀገራት ጉባዔ ላይ ለመካፈል ነው፡፡
በጉባዔው ላይ የአህጉሩ ቀዳሚ ቡና አምራች የሆነችው ኢትዮጵያን ጨምሮ፤ 25 የአፍሪካ ቡና አምራች ሀገራት እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡
”የአፍሪካ የቡና ኢንዱስትሪን በማነቃቃት ለወጣቶች የሥራ ዕድሎችን መክፈት” በሚል መሪ ሐሳብ ነው ጉባዔው የሚካሄደው፡፡
በጉባዔው ላይ ዘርፉን ለማነቃቃትና ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችሉ ውይይቶች እንደሚደረጉ ይጠበቃል፡፡