Fana: At a Speed of Life!

ብልፅግና ፓርቲ ጉባኤው ባሳለፋቸው ውሳኔዎች ላይ ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብልጽግና ፓርቲ በ2ኛ መደበኛ ጉባኤው ባሳለፋቸው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ዙሪያ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

የፓርቲው የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥ ፓርቲው በ2ኛ ጉባኤው የዜጎችን ተጠቃሚነት ከፍ የሚያደርጉ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

የዛሬው ውይይትም በውሳኔዎች እና አቅጫዎች ላይ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡና ለዓለም አቀፍ ተቋማት የተደራጀ መረጃ ለመስጠት ያለመ ነው ብለዋል።

በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ቁልፍ አጀንዳዎች ላይ መግባባት ለመፍጠር ውይይቱ ትልቅ ሚና እንዳለውም ጠቁመዋል።

የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ነብዩ ስሁል፥ የፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ እና ያሳለፋቸው አቅጫዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል።

ፓርቲው በሰጠው አመራር በየመስኩ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ጠቅሰው፥ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ፣ የዘርፎች ሪፎርም፣ በምግብ ራስን የመቻል እንዲሁም የትላልቅ ፕሮጀክት ግንባታ አፈጻጸምን በአብነት ጠቅሰዋል።

በቀጣይም ጠንካራ ፓርቲ መገንባት፣ አንድ የሚያደርጉ አሰባሳቢ ትርክቶችን መፍጠር፣ ዘላቂ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን ማጠናከር ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ወደ ሥራ መግባቱንም መናገራቸውን የብልጽግና ፓርቲ መረጃ አመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.