ፕሬዚዳንት ታዬ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ አምባሳደሮች አሰናበቱ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የኢንዶኔዥያ አምባሳደር አልቡሲራ ባስኑርን እና የካዛኪስታን አምባሳደር ባርሊባይ ሳዲኮቭን አሰናበቱ።
አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ላደረጉት አስተዋፅኦፕሬዚዳንቱ አመሥግነዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር ያላትን ትብብር ይበልጥ የሚያጎለብቱ የተለያዩ ስምምነቶች እንዲፈረሙ ማድረጋቸውንም አውስተዋል።
በዚህም በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በትምህርት፣ በኢንቨስትመንት እና በሌሎች ዘርፎች ጠንካራ ትብብር ተፈጥሯል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አምባሳደሮቹ በበኩላቸው ሀገሮቻቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በተለያዩ መስኮች ይበልጥ እንዲሰፋ የበኩላቸውን ሚና እንደሚበረክቱ ተናግረዋል።