የኢሉ ገላን የሙዝ ኢኒሼቲቭን ወደ 27 ሺህ ሔክታር ማሳደግ ተቻለ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2012 ዓ.ም በ70 ሔክታር ላይ የተጀመረውን የሙዝ ምርጥ ዘር ልማት አሁን 27 ሺህ ሔክታር ማድረስ መቻሉን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡
ርዕሰ መሥተዳድሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባጋሩት ጽሑፍ፤ በዚህ ሥራ የተሳፉ አካላትን አመሥግነዋል፡፡
የሥራ ዕድል ከመፍጠርና በምግብ ራስን ለመቻል በሚደረገው ጥረት ኢኒሼቲቩ አበርክቶው ከፍ ያለ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በ2016 ዓ.ም የሙዝ ምርትን ወደ ውጪ በመላክ የክልሉን የወጭ ንግድ ማሳደግ መቻሉን አውስተዋል፡፡
እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ 40 ሺህ ሔክታር ለማድረስ እየተሠራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡