Fana: At a Speed of Life!

ለሆሳዕና ከተማ ኮሪደር ልማት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሆሳዕና ከተማ ኮሪደር ልማትና ለሌሎች ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የዞኑ ተወላጅ ባለሃብቶች ተሳትፈዋል፡፡

በሆሳዕና ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራ እንዲሁም ሌሎች ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብርም የፕሮጀክቶችን ግንባታ ለማጠናቀቅ የሚያግዝ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

በመንግሥት ወጪ ብቻ የማይሸፈኑ የልማት ፕሮጀክቶችን ማህበረሰቡን በማሳተፍ ፈጣንና ሁለንተናዊ ለውጥ ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.