Fana: At a Speed of Life!

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍን ለማሳደግ በመተባበር መስራት ይገባል – ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢኮኖሚው ደም ስር የሆነውን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍን ለማሳደግ በመተባበር መስራት ይገባል ሲሉ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም ሀገር አቀፍ ሴክተር ጉባኤ መድረክ ላይ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ ባስመዘገበችው የኢኮኖሚ ዕድገት ዘርፉ የአስቻይነት ሚና ቢጫወትም አሁንም ብዙ ሥራዎች እንደሚቀሩ ተናግረዋል።

ለዚህም ባለድርሻ አካላት በመተባበር በቅርበት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ሪፖርቱን ያቀረቡት የሚኒስቴሩ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ ዮሐንስ ቢሻው፤ የአዳዲስ አውሮፕላን ማረፊያዎች ግንባታና የነባር አውሮፕላን ማረፊያዎች ማስፋፊያ የተሻለ አፈጻጸም ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ11 ሚሊየን በላይ ዓለም አቀፍ መንገደኞችን እና 2 ነጥብ 9 ሚሊየን የሀገር ውስጥ መንገደኞችን ማጓጓዙን ጠቁመዋል።

በመሳፍንት እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.