አመራሩ ሕዝብን በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት ለማገልገል መዘጋጀት አለበት – አቶ ሙስጠፌ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በየደረጃው ያለ አመራር ሕዝብን በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት ለማገልገል ከመቼውም ጊዜ በላይ መዘጋጀት አለበት አሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ፡፡
በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና በአፍሪካ አመራር ልቀት አካዳሚ ለክልሉ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቅቋል።
አቶ ሙስጠፌ በዚህ ወቅት ÷ የለውጡን መልካም ጅምሮችና እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶችን የሚያስቀጥል ጠንካራ አመራር እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
አመራሩ ከምንም በላይ ሕዝብን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል እንዳለበት የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ ለዚህም በእውቀት የሚመራ ሙሉ ፍላጎትና ዝግጁነት ያለው አመራር ሊኖር ይገባል ብለዋል፡፡
በመሆኑም በየደረጃው ያለ አመራር ሕዝብን በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት ለማገልገል ከመቼውም ጊዜ በላይ መዘጋጀት አለበት ሲሉ አሳስበዋል።
በሁሉም ዘርፎች አሁን ላይ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ እየታገዙ፣ በእውቀት የሚመሩና በብቃትና ክህሎት የሚሰጡ በመሆኑ ከጊዜው ጋር እውቀትንና ብቃትን ማሳደግ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡
በክልሉ በሁሉም መስኮች አስደናቂ የልማት ሥራዎችና ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ጠቅሰው÷ የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና በትኩረት እንደሚሰራ ማስገንዘባቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!