Fana: At a Speed of Life!

የኃይልና መሰረተ ልማት ስርቆትን ለማስቀረት የፖሊሲ እና አሰራር ማሻሻያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኃይልና መሰረተ ልማት ስርቆትን ለማስቀረት የፖሊሲ እና አሰራር ማሻሻያ አድርጓል።

አገልግሎቱ ባለፉት ጊዜያት የኃይል እና መሰረተ ልማት ስርቆትን ለማስቀረት ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን ገልጿል።

በአገልግሎቱ የህግ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ አበበ ተስፋ በበጀት ዓመቱ 239 የመሰረተ ልማት ስርቆት ወንጀሎች መፈጸማቸውን ገልጸዋል።

በዚህም በመሰረተ ልማቶቹ ጉዳት ያደረሱ 24 ግለሰቦች በፍርድ ቤት ጥፋተኛ መሆናቸው ተረጋግጦ ከ4 ወር እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት መቀጣታቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከ5 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን አንስተው÷ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሱ የስርቆት ወንጀሎች አገልግሎቱን በአግባቡ ተደራሽ ለማድረግ ተግዳሮት መሆኑን ተናግረዋል።

በአዲሱ የፖሊሲ እና አሰራር ማሻሻያ መሰረት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት ወንጀል ላይ ተሰማርቶ የተገኘ ማንኛውም ሰው ከ5 እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ አስገንዝበዋል።

የአገልግሎቱ የሽያጭና ደንበኛች አገልግሎት ዳይሬክተር ይሄይስ ስዩም በበኩላቸው÷ ባለፉት 11 ወራት 298 የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት መፈጸሙን ጠቁመው÷ በዚህም 259 ሚሊየን ብር ኪሳራ መከሰቱን አስረድተዋል።

ከመኖሪያ ቤቶች እስከ ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች የኃይል ስርቆት እንደሚፈጸም ገልጸው÷ ወንጀሉን ሲፈጽሙ በተገኙ ላይ ከ20 ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋልም ብለዋል።

መሰል ወንጀሎች ሲፈጸሙ ጥቆማ ለሚሰጥ የማህበረሰብ አካል የ25 በመቶ ኮሚሽን እንደሚሰጣቸውና ህብረተሰቡም የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ተጠይቋል።

በአቤል ንዋይ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.