ድሬዳዋ ከተማ በፕሪሚየር ሊጉ መቆየቱን አረጋገጠ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ስሑል ሽረን በማሸነፍ በሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል፡፡
በ35ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር በወንጂ ሁለገብ ስታዲየም ከሊጉ መውረዱን ያረጋገጠውን ስሑል ሽረን የገጠመው ድሬዳዋ ከተማ 4 ለ 2 አሸንፏል፡፡
የድሬዳዋ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች መስዑድ መሐመድ (2) እንዲሁም ዮሀንስ ደረጀ እና ሀቢብ ከማል አስቆጥረዋል፡፡
የስሑል ሽረን ግቦች ብርሃኑ አዳሙ እና አላዛር ሽመልስ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ ነጥቡን 43 በማድረስ በቀጣዩ የውድድር አመት በፕሪሚየር ሊጉ እንደሚቆይ አረጋግጧል፡፡