Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የአቮከዶ ችግኝ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የአቮከዶ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ ተደርጓል አለ።

በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክልሉ የአቮካዶ ምርታማነትን ለማሳደግ በ30-40-30 ኢኒሼቲቭ እና በመደበኛ ፕሮግራም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፡፡

በዚህም አቮካዶ ተስማሚ እና ምርታማ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት በ44 ወረዳዎች የአቮካዶ ምርትን ለማሳደግ በትኩረት እየሰተራ መሆኑን ገልጸው÷ በየዓመቱ በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በርካታ ችግኞች እየተተከሉ መሆናቸውን አንስተዋል።

ለሕብረተሰቡ የሃብትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ጠቁመው÷ በርካታ ወጣቶች ችግኞችን በማባዛት ሥራ በመሳተፍ የተሻለ ገቢ እያገኙ ነው ብለዋል፡፡

የመንግስት እና የሃይማኖት ተቋማት የፍራፍሬ ማዕከል እንዲሆኑ ለማስቻል ባሏቸው ቦታዎች ከ100 እስከ 10 ሺህ ችግኞችን እንዲተክሉ በመግባባት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተከናወነው ሥራም ባለፈው ዓመት በአንድ ጀምበር እስከ 10 ሺህ ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰው ÷ በዘንድሮው ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

በሌላ በኩል የአቮካዶ ምርት የውጭ ምንዛሪ ምንጭ እየሆነ እንደሚገኝ ጠቁመው÷ በክልሉ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ የውጪ የመላክ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.