Fana: At a Speed of Life!

የሎጂስቲክስ ዘርፉን የሚያሳልጥ የማሻሻያ ሥራ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሎጂስቲክስ ዘርፉን ማሳለጥ የሚያስችሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው አለ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፡፡

በሀገር ውስጥ አስመጪና ላኪ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች የሚገጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ እንደ ሀገር እየተመዘገበ ለሚገኘው የኢኮኖሚ እድገት የዘርፉ ባለሃብቶች አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡

በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት በትራንስፖርት ዘርፍ ያሉትን ችግሮች መፍታት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የጊዜ አጠቃቀም ነጋዴውን ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚው እድገት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ችግሩን ለመፍታት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የአገልግሎት ዘርፉን የሚያሳልጡ በርካታ ማሻሻያዎችን እያደረገ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

የትራንስፖርት ዘርፍ ብሔራዊ ጥቅምን ከሚያስከብሩ ዘርፎች አንዱ ነው ያሉት ሚኒስትሩ÷አገልግሎቱን ቀልጣፋ እና ዘመናዊ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቅሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ በአስመጪ እና ላኪነት የተሰማሩ የግል ባለሃብቶች የሚገጥማቸውን ችግር ለመፍታት በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

አሁን ላይም ተቋማቸው የሚጠቀምበትን የማኑዋል ሥርዓት ወደ ዲጂታል ለመቀየር እየተሰራ መሆኑን አስገዝበዋል፡፡

በሚልኪያስ አዱኛ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.