Fana: At a Speed of Life!

ሊቨርፑል ሚሎሽ ኬርኬዝን ከበርንማውዝ አስፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሊቨርፑል የግራ ተመላላሽ ተጫዋች የሆነውን ሚሎሽ ኬርኬዝ ከበርንማውዝ አስፈርሟል፡፡

ኬርኬዝ የሕክምና ምርመራውን በተሳካ ሁኔታ ካለፈ በኋላ ከሊቨርፑል ጋር የ5 ዓመት ውል መፈረሙ ተመላክቷል።

ለተጫዋቹ ዝውውር ሊቨርፑል 40 ሚሊየን ፓውንድ ማውጣቱ ነው የተገለጸው፡፡

የ21 ዓመቱ ሀንጋሪያዊ ከሆላንዳዊው ጄረሚ ፍሪምፖንግ፣ ሌላኛው ሀንጋሪያዊ አርሚን ፔክሲ እና ጀርመናዊው ፍሎሪያን ሸርትስ በመቀጠል አራተኛው የሊቨርፑል ፈራሚ ተጫዋች ሆኗል፡፡

ለሊቨርፑል ፊርማውን ካኖረ በኋላ ሚሎሽ ኬርኬዝ በሰጠው አስተያየት÷ “ለፕሪሚየር ሊጉ ኃያል ክለብ” በመፈረሙ ደስተኛ መሆኑን ገልጿል፡፡

በሊቨርፑል ቆይታው ለክለቡ የሚችለውን ሁሉ ለማድርግ ቁርጠኛ መሆኑንም ተናግሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.