Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በፍራፍሬ ልማት ኢኒሼቲቭ ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ባለው የ30-40-30 የተቀናጀ የፍራፍሬ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ ተግባራት ተከናውኗል አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ።

በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር÷ ኢኒሼቲቩ ለሕብረተሰቡ በተለይም ለወጣቶች ሰርተው የሚለወጡበትን እድል በመፍጠር ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢኒሼቲቩ ስድስት ጉዳዮችን ትኩረት አድርገን ሥራውን ጀምረናል ያሉት አቶ ኡስማን ÷ እነዚህም የምግብና ሥነ ምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ ማረጋገጥ፣ የገቢ ምርትን መተካት፣ የውጪ ምርትን ማሳደግ፣ ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ በቂ ግብዓት ማቅረብ፣ በሒደቱ ለዜጎች የስራ እድል መፍጠር እና ከድህነት የተላቀቀ ወደ ብልጽግና ማማ ከፍ ያለ ቤተሰብ፣ ማህበረሰብ፣ ክልል ብሎም ሀገር መፍጠር መሆናቸውን አብራርተዋል።

በዚህም አቮካዶ፣ ሙዝ፣ ፓፓያ፣ አፕል እና ማንጎ ፍራፍሬዎች በክልሉ በሚገኙ 53 ወረዳዎች እንደየአካባቢው አየር ሁኔታ መብቀል የሚችሉበትን ቦታዎች የመለየት ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡

በተሰራው ሥራም 44 አቮካዶ፣ 24 ፓፓያ፣ 16 አፕል፣ 40 ማንጎ እና 32 ሙዝ ማምረት የሚችሉ ወረዳዎች መለየት መቻሉን ነው ያነሱት።

በዚህም ፍራፍሬዎቹን አምርተው በማያውቁ አካባቢዎች ጭምር ሐሳቡን በመተግበር በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎች አምርተው መጠቀም፣ የተፈጠረውን ፍላጎት መነሻ በማድረግ ችግኞችን አብዝቶ በመሸጥ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን አስረድተዋል፡፡

ኢኒሼቲቩ በአካባቢዎቹ አዲስ ዕይታ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ የአመራረት ሥርዓት እና አዳዲስ ውጤቶችን ይዞ መምጣቱን አቶ ኡስማን ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

በተጨማሪም የፍራፍሬ ምርቶቹ ለኢንዱስትሪ ግብዓትና ለተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሥራ ዕድል ፈጠራና የገቢ ምንጭ እንዲሆን ለማስቻል ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱንና ውጤታማነቱ እየተረጋገጠ መሆኑንም አመልክተዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.