በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ፈተና ማዕከላት እየገቡ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ወደ ፈተና ማዕከላት እየገቡ ነው አለ የክልሉ ትምህርት ቢሮ።
በቢሮው የትምህርት ምዘናና ፈተና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ታገሰ ለፋና ዲጂታል እንደገለጹት፤ ዘንድሮ 35 ሺህ 246 የክልሉ ተማሪዎች ሀገር አቀፉን የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ።
ከሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች ወደ ተዘጋጁ የፈተና ማዕከላት መግባት መጀመራቸውን ተናግረዋል።
ለ35 ሺህ 246 ተማሪዎች በወረቀት እና በበይነ መረብ ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል በቂ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።
በበይነ መረብ ፈተና ለሚወስዱ 7 ሺህ 211 ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች እና በአዳሪ ትምህርት ቤቶች ዘጠኝ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ገልጸው፤ ተማሪዎቹ ስለ ፈተና አሰጣጡ ስልጠና ማግኘታቸውን አስታውሰዋል።
በወረቀት የሚፈተኑ 28 ሺህ 35 ተማሪዎች ደግሞ በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ልምምድ አድርገዋል ብለዋል።
በወረቀት የሚፈተኑ ሁሉም ተማሪዎች ፈተውን የሚወስዱት በዩኒቨርሲቲዎች ብቻ መሆኑንም አመላክተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!