Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ የአፈር ማዳበሪያ ከውጭ ማስገባት ታቆማለች – አሊኮ ዳንጎቴ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሚቀጥሉት 40 ወራት ውስጥ አፍሪካ የአፈር ማደባሪያ ከውጭ ማስገባት ታቆማለች አሉ ናይጀሪያዊው ባለሃብት አሊኮ ዳንጎቴ፡፡

ባለሃብቱ በናይጀሪያ አቡጃ በተካሄደው አፍሪኤክሲም ባንክ ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት÷ አፍሪካውያን የአፈር ማዳበሪያ ከውጭ የሚያስገቡ በመሆኑ ለከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ጫና ተዳርገዋል።

አፍሪካ በአፈር ማዳበሪያ ምርት ራሷን እንድትችል ለማድረግ ኩባንያቸው 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በጀት በመመደብ ወደ አፈር ማዳበሪያ ሊገባ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

ይህም የአፍሪካ ሀገራትን የአፈር ማዳበሪያ ፍጆታ ማሟላት እንደሚያስችል ገልጸው÷ አፍሪካውያን በሚቀጥሉት 40 ወራት ውስጥ የአፈር ማዳበሪያ ከውጭ ማስገባት ያቆማሉ ብለዋል፡፡

የአፈር ማዳበሪያን በሀገር ውስት ማምረት መጀመር የውጭ ምንዛሬ ጫናን ከማስቀረት በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ያለውን የተጋነነ ዋጋ ለማስተካከል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አመልክተዋል።

የሀገር ውስጥ አቅምን ማሳደግ የአፍሪካን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እንዲሁም የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ነው ያስገነዘቡት፡፡

ኩባንያቸው የሚያመርተው የአፈር ማዳበሪያ በፈረንጆቹ 2025 መጨረሻ በናይጄሪያ የአክክሲዮን ገበያዎች ላይ መሸጥ እንደሚጀምርም መግለጻቸውን ጋና ዌብ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.