Fana: At a Speed of Life!

ጆርጅ ኤሎምቢ የአፍሪኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት ሆኑ ‎

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የካሜሩን ዜግነት ያላቸው ጆርጅ ኤሎምቢ የአፍሪካ ኤክስፖርት ኢምፖርት (አፍሪኤግዚም) ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።

‎ተመራጩ ፕሬዚዳንት የባንኩን የዳይሬክተሮች ቦርድ በሊቀመንበርነት ይመራሉ።

‎ኢሎምቢ የተመረጡት ባንኩን ላለፉት 10 ዓመታት በፕሬዚዳንትና የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር የነበሩትን ቤኔዲክት ኦራማህ (ፕ/ር) በመተካት ነው።

‎በባንኩ ባለድርሸዎች ጠቅላላ ጉባዔ የተመረጡት ኤሎምቢ ባንኩን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እና በተለያዩ ደረጃዎች ላለፉት 20 ዓመታት ማገልገላቸው ተገልጿል።

ኤሎምቢ ከተመሠረተ 32 ዓመታት ያስቆጠረውን ባንክ ለመምራት አራተኛው ፕሬዚዳንት ሆነዋል ሲል የባንኩ መረጃ አመልክቷል።

የባንኩ ሦሰተኛ ፕሬዚዳንት ሆነው ያገለገሉት ቤኔዲክት ኦራማህ (ፕ/ር) ባንኩን ወደላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር አድርገዋል ተብሏል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.