Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 150 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በበጀት ዓመቱ 150 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርቧል።

የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማሪያም ሰጠኝ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ክልሉ የወርቅና ድንጋይ ከሰል ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በበጀት ዓመቱ 300 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ለማቅረብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አንስተው÷ እስካሁን 150 ኪሎ ግራም ወርቅ ማቅረብ መቻሉን ጠቁመዋል።

ዕቅዱን ማሳካት አለመቻሉን ጠቁመው÷ በዘርፉ የተስተዋለው ሕገ ወጥ ንግድ እና ፈቃድ የወሰዱ አምራቾች በሚጠበቅባቸው ልክ ወደ ስራ አለመሰማራታቸው ለአፈፃፀሙ ተግዳሮት መሆናቸውን አብራርተዋል።

ይህንንም ችግር ለመቅረፍ አዳዲስ ቦታዎች ላይ ለአምራቾች ፈቃድ መስጠትና ሕገ ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር ግብረ ኃይል በማቋቋም የቁጥጥርና ክትትል ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ፍቃድ የተሰጣቸው ወርቅ አቅራቢዎች፣ ባህላዊ ወርቅ አምራች ማህበራት እና ልዩ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚያገኙትን ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ የማስገባት ስራ ማጠናከር አለባቸው ነው ያሉት።

በሌላ በኩል በተያዘው በጀት ዓመት ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚውል 168 ሺህ ቶን የከሰል ድንጋይ ማቅረብ መቻሉን አመልክተዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.