Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የኮሪደር ልማት እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የከተማ ኮሪደር ልማት ሥራ በተቀናጀ መንገድ እየተከናወነ ይገኛል።

የክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ በክልሉ 18 ከተሞች የኮሪደር ልማት ስራ ተጀምሯል።

በአርባ ምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ዲላ፣ ሳውላ፣ ይርጋጨፌ፣ ጊዶሌ፣ ጂንካ፣ ገደብ፣ አረካ እና ሁምቦ ጸበላ ከተሞች የአካባቢውን ሕብረተሰብ በማሳተፍና በመንግስት ወጪ የኮሪደር ልማቱ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በዚህም 39 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር የተሽከርካሪ፣ 46 ኪሎ ሜትር የእግረኛ እና 18 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገዶች እየተሰሩ እንደሆነ ጠቁመዋል።

እንዲሁም 105 ሄክታር የመንገድ ዳር አረንጓዴ ልማት እና 13 ኪሎ ሜትር የመናፈሻ ቦታዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

መንግስት 1 ነጥብ 98 ቢሊየን ብር የሸፈነ ሲሆን ሕብረተሰቡ ደግሞ 722 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት፣ ጉልበትና ጥሬ ገንዘብ አስተዋጽዖ በማድረግ በአጠቃላይ ከ2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የኮሪደር ልማቱ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

የኮሪደር ልማቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት ጋር በመሆን በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም አመላክተዋል።

የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በሁሉም የክልሉ ከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.