ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ከ76 ቢሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ከ76 ቢሊየን ብር በላይ ተሰብስቧል አለ።
የሚኒስቴሩ የ2017 በጀት አመት አፈፃፀምን እንዲሁም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን የሚገመግም መድረክ አካሂዷል፡፡
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በመድረኩ ባቀረቡት ሪፖርት÷ ሚኒስቴሩ በብዙ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ ዘርፉን በተሻለ ደረጃ ለመምራት የሚያስችሉ በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ተጨባጭ ውጤት ማምጣቱን አንስተዋል፡፡
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የአሠራርና አደረጃጀት ሥርዓት ባለፉት ዓመታት መሻሻል ማሳየቱ እና ትላልቅ የመሰረተ ልማት ኘሮጀክቶችን ለመፈፀም የሚያስችል ልምድ በሰፊው እየዳበረ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ 175 ሺህ 879 ኪሎ ሜትር የመንገድ መሠረተ ልማት አውታር ሽፋን ማድረስ መቻሉን እንዲሁም የመዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ደረጃን በ220 ከተሞች መተግበር መቻሉን ገልጸዋል፡፡
የከተማ አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የከተሞች የፕላን ዝግጅት ቁጥር ወደ 88 ነጥብ 7 ከፍ እንዲል ማድረግ መቻሉንም አስገንዝበዋል፡፡
ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በ2017 ዓ.ም 76 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉ አንስተው በዚህም የከተሞች መሠረተ ልማት ወኚያቸውን 51 ነጥብ 1 በመቶ መሸፈን ተችሏል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም 499 ሺህ 75 የመሬት ይዞታ በካዳስተር ስርዓት ስር መመዝገቡን ጠቁመዋል፡፡
በቤዛዊት ከበደ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!