እስራኤል በጋዛ ለ60 ቀናት የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማማች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እስራኤል በጋዛ የ60 ቀናት የተኩስ አቁም ማድረግ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎችን ለማከናወን ተስማምታለች አሉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ አሜሪካ በጋዛ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም ከሁሉም አካላት ጋር በቅርበት ትሰራለች ብለዋል።
ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንደሚቀበል ተስፋ አለኝ ያሉት ፕሬዚዳንቱ ÷ ሃሳቡን የማይቀበል ከሆነ ግን ችግሩ ተባብሶ ሊቀጥል እንደሚችል አስገንዝበዋል፡፡
እስራኤል በተኩስ አቁም ሒደቱ ዙሪያ መስማማቷን ባታረጋግጥም የሃማስ ባለስልጣናት ግን ጦርነቱን ለማቆም የሚያስችሉ መስፈርቶች ከተሟሉ ለመስማማት ዝግጁ እንደሆኑ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳአር በበኩላቸው በመንግስት ውስጥ ታጋቾችን ለመልቀቅ የሚያስችል ከፍተኛ ድጋፍ መኖሩን ጠቅሰው÷እድሉን በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብለዋል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!