የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ስለሚያረጋግጡ ተጠናክረው ይቀጥላሉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የማህበረሰቡን ኑሮ በመቀየር ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ሥራዎች በመሆናቸው ተጠናክረው ይቀጥላሉ አሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)።
ርዕሰ መስተዳድሩ ‘በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ’ በሚል መሪ ሐሳብ የሚካሄደውን ክልላዊ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በቦንጋ ከተማ ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፤ በጎ ፍቃድ አገልግሎት የመተሳሰብ እና ያለውን የመካፈል እሴት የሚያላብስ ነው ብለዋል።
ባለፉት ዓመታት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአረጋውያን ቤት በማደስ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በአካባቢ ንጽሕና መጠበቅ፣ በአረንጓዴ አሻራ እና በሌሎች መሠል የማህበረሰቡን ህይወት በሚቀይሩ ሥራዎች ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጠቀሜታን በመገንዘብ ለስኬታማነቱ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ርዕሰ መስተዳድሩ ማስገንዘባቸውን የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ የሺዋስ ዓለሙ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ በበኩላቸው በዘንድሮ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ14 የትኩረት መስኮች 1 ሚሊየን 33 ሺህ ህብረተሰብ ክፍል ለማሳተፍ መታቀዱን ጠቁመዋል።
በተግባሩም 2 ነጥብ 4 ሚሊየን የሕብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ነው ያመላከቱት።
በዚህም 980 ሚሊየን ብር የሚገመት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!