Fana: At a Speed of Life!

ከ265 ሺህ በላይ የመኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሁኑ ወቅት ከ265 ሺህ በላይ የመኖሪያ ቤቶች በግንባታ ሒደት ላይ ናቸው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከም/ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ÷ የለውጡ መንግስት የዜጎችን የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዚህ መሰረትም የቤት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት በመንግስት፣ በግል እንዲሁም በመንግስትና በግል አጋርነት እየተሰራ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት፡፡

ይህን ተከትሎም ባለፉት ዓምስት ዓመታት 1 ሚሊየን የሚጠጉ ቤቶች መገንባታቸውን አስታውሰው÷አሁን ለይ ከ265 ሺህ በላይ ቤቶች እየተገነቡ ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡

በሌላ በኩል በክረምት በጎ ፈቃድ ከ100 ሺህ ያላነሰ ቤቶችን መገንባት መቻሉን ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ በዘርፉ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ሥራው በከተማ ብቻ ሳይሆን በገጠርም የገጠር ኮሪደር ልማትን በማስጀመር ጽዱና ውብ አካባቢን ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡

 

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.