የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 3ኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
በፎረሙ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ፣የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች፣ የፈጠራ ባለሙያዎችና የዘርፉ ምሁራን ተሳትፈዋል፡፡
ፎረሙ ላለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት እንደ አህጉር ያለውን እምቅ ሃብት ወደ ተጨባጭ አቅም ለመቀየር ዕድል በሚፈጥር መልኩ መካሄዱ ይታወሳል፡፡
በዚህም በሚሊየን የሚቆጠሩ የአህጉሪቱ ወጣቶች ምቹና ዘላቂ የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ነው የተመላከተው፡፡
ፎረሙ ነባራዊ ሁኔታን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የወጣቶችን አቅም ለማጎልበትና ዕድሎችን ለመጠቀም አቅም የሚፈጥር ሲሆን÷ የዘንድሮው ፎረም በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ላይ ትኩረቱን ያደርጋል፡፡
ለሦስተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከዛሬ ጀምሮ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የሚካሄደው መድረኩ እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!