በቴክሳስ የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 82 ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ባለፈው ሳምንት አርብ በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 82 ደርሷል፡፡
በግዛቲቱ በተለያዩ አካባቢዎች በደረሰው የጎርፍ አደጋ ከሞቱ ሰዎች መካከል 28ቱ ህጻናት መሆናቸው ነው የተነገረው፡፡
በአደጋው ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ በርካታ ሰዎች መጥፋታቸው የተገለጸ ሲሆን፥ የነፍስ አድን ስራዎች መቀጠላቸውን የቴክሳስ ግዛት ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
የሀገሪቱ የአየር ሁኔታ አገልግሎት እንዳስታወቀው፥ በማዕከላዊ ቴክሳስ በሚገኙ አካባቢዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጥል ይጠበቃል፡፡
ይህን ተከትሎም በቀጣይ ሰዓታት መሰል የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ማስጠንቀቁን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡