Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለ366 ሺህ ወጣቶች ቋሚ የሥራ እድል ተፈጠረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለ366 ሺህ ወጣቶች ቋሚ የሥራ እድል ተፈጥሯል አለ የከተማዋ ሥራና ክህሎት ቢሮ።

በም/ከንቲባ ማዕረግ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ እንዳሉት ÷ መንግስት ባለፉት ዓመታት ለዜጎች ቋሚ የሥራ እድል ለመፍጠር ሲሰራ ቆይቷል።

በ2017 በጀት ዓመት መጀመሪያ በአዲስ አበባ ለ300 ሺህ ሥራ ፈላጊዎች በፍትሃዊነት የሥራ እድል ለመፍጠር እቅድ ተይዞ ወደ ሥራ መገባቱን አስታውሰዋል፡፡

በዚህም ቢሮው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ከሆኑ ሥራ ፈላጊ ወጣቶችና ወላጆች ጋር ውይይት ማድረጉን ጠቅሰዋል።

ሥራ ፈላጊዎችን በፍትሃዊነት ለመቀበል በተከናወነው ሥራ 403 ሺህ ዜጎችን በኦን ላይን በመመዝገብ በበጀት ዓመቱ ለ366 ሺህ 44 ወጣቶች ቋሚ የሥራ እድል መፍጠር መቻሉን አመልክተዋል፡፡

ለወጣቶቹ በከተማ ግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በንግድና ሌሎች ዘርፎች የሥራ እድል በመፍጠር በቅጥርና በማደራጀት ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉንም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.