Fana: At a Speed of Life!

ጥራት ያለው የዳኝነት አገልግሎትን የሚሰጥ የፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት እየተሰራ ነው – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የሕግ የበላይትን የማረጋገጥ እና ጥራት ያለው የዳኝነት አገልግሎትን የሚሰጥ የፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት እየተሰራ ነው አሉ።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕንጻ እና የዲጂታላይዜሽን ምረቃ ሥነ ሥርዓት በባሕርዳር ተካሂዷል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሳደግ ከሚሰሩ ሥራዎች መካከል የተቋም ግንባታ በልዩ ትኩረት እየተከናወነ ነው።
በሰው ኃይል ልማት፣ የተቋም አደረጃጃት ማሻሻል እና ፍርድ ቤቶች ከሌሎች ተቋማት ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማሳደግ ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን አብራርተዋል፡፡
የዳኝነት ሥርዓቱን በሒደትም ሆነ በውጤት የማሻሻል ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው÷ የላቀ የፍትሕ አገልግሎት በሚል ተደራሽ፣ ተገማች እና የሕዝብ እርካታ በሚያሳድጉ ሥራዎች ለይተን እየሰራን ነው ብለዋል።
የአማራ ከልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕንጻ እና የዲጂታላይዜሽን ሥራም የተቋም ግንባታው አንድ አካል ነው ብለዋል።
የምናገለግለው ሕዝብ በብዙ ችግሮች ውስጥ ስለሆነ በታላቅ ትጋት እና በትብብር ልናገለግል ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድስ ምህረት በበኩላቸው ÷ ዜጎች በግልጽ ችሎት የመዳኘት ህገ መንግስታዊ መብታቸው እንዲከበር ለማድረግ የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በሃገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የፍትህ መስፈን፣ የህግ የበላይነት መረጋገጥ፣ ነጻ ገለልተኛ እና ጥራቱን የተጠበቀ ፍትህ የሚሰጡ የፍትህ ተቋማት ያስፈልጋሉ ነው ያሉት።
በለይኩን ዓለም
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.