Fana: At a Speed of Life!

አዋጁ የስራ ስምሪት ሂደት ላይ ያለውን የደላሎችን ህገ ወጥ ድርጊት ያስቀራል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲሱ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አዋጅ የስራ ስምሪት ሂደት ላይ ያለውን የደላሎችን ህገ ወጥ ድርጊት ያስቀራል አለ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር፡፡
በውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት የነበሩ ክፍተቶችን እንደሚሞላ የታመነበት የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር1389/2017 ከሰሞኑ መጽደቁ ይታወሳል።
በሚኒስቴሩ የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤርሚያስ ተክሉ እንዳሉት፥ አዋጁ ዜጎች መብታቸው ተከብሮና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ያስችላል።
እንዲሁም በስራ ስምሪት ሂደቱ ላይ ያለውን የደላሎችን ህገ ወጥ ድርጊት የሚያስቀር ነው ብለዋል፡፡
ዜጎች በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት በኩል ያለምንም የደላላ ንክኪ ምዝገባና ሌሎችንም አስፈላጊ መረጃዎች የሚሞሉበት አሰራርን ያመቻቸ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
አዋጁ የስራ እድል አማራጮችን ከማስፋትም ባሻገር ሀገሪቱ ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ገቢ በአግባቡ እንድታገኝ ያስችላል ብለዋል፡፡
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የህግ ክፍል ኃላፊ ወ/ሮ ሲቲና መንግስቱ በበኩላቸው፥ አዲሱ አዋጅ የዜጎች መብት ደህንነትና ክብርን ለማስጠበቅ የሚረዳ መሆኑን ጠቅሰው፥ የዋስትና ገንዘብንም በተመለከተ በአዋጁ መካተቱን አንስተዋል።
በፌቨን ቢሻው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.