በቁልቢ የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በየዓመቱ ሐምሌ 19 በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊው የንግስ በዓል ዘንድሮም በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በቅዳሴ፣ በዝማሬ፣ በፀሎትና በሌሎች ሃይማኖታዊ ስነ ሥርዓቶች ነው በታላቅ ድምቀት እየተከበረ የሚገኘው።
ለበዓሉ ስኬታማነትም የፀጥታ አካላት፣ የአካባቢው ማህበረሰብና የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በቅንጅት እየሰሩ ናቸው።
እየተከበረ በሚገኘው ዓመታዊ የንግስ በዓል ስነ ሥርዓት ላይ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም ከውጭ ሀገራት የመጡ ምዕመናን ተገኝተዋል።
በተስፋዬ ኃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!