Fana: At a Speed of Life!

የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ በ2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ አመሻሹን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ቀደም ሲል የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ እንዲሁም የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.