የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዓለም አንድ ላይ የሚቆምበት ወቅት ነው – ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዓለም አንድ ላይ የሚቆምበት ወቅት ነው አሉ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ፡፡
ኢትዮጵያ ከጣሊያን እና ከተባበሩት መንግስታት ጋር በመተባበር ያዘጋጀችው 2ኛው የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በጉባኤው ላይ የተገኙት የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ፤ የምግብ ስርዓታችን የማይገመትና በፈተና ውስጥ ያለ በመሆኑ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዓለም አንድ ላይ የሚቆምበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል፡፡
ቀጣይነት ያለው፣ የማይበገርና ሁሉንም አካታች የሆነ የምግብ ስርዓት ለማረጋገጥ በጋራ መስራት አለብን ነው ያሉት።
የአየር ንብረት ለውጥ፣ ድርቅ፤ ግጭትና ያልተመጣጠነ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የምግብ ስርዓቱንና የምግብ አመራረታችንና አጠቃቀም ፍላጎታችንን ማሟላት ባለመቻሉ ክፍተቱን ለመሙላት የበለጠ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉም ገልጸዋል።
ግብርና ለሶማሊያ ስራ ብቻ ሳይሆን የደም ስሯ፣ ህልውናችን፣ ባህላችንና የመኖር ዋስትናችን ጭምር ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ÷ ሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የምታገኘው ከግብርና ቢሆንም የአየር ንብረት ለውጥና ሌሎች ተደራራቢ ማህበራዊ ቀውሶች ህዝባችንን ለመመገብ የምናደርገውን ጥረት አዳጋች አድርጎብናል ብለዋል፡፡
የቁም እንስሳት ዘርፉ ለሶማሊያ ግብርና ዘርፍ ካለው አስተዋጽኦ ባሻገር ለሶማሊያዊያን የምግብ ዋስትና መረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ነው የገለጹት፡፡
የሰብል ምርታማነትንንና የእንስሳት ልማትን በማቀናጀት በገጠር የሚኖሩ ዜጎቻችንን ህይወት ማሻሻል ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
ሀገሪቱ በጀመረችው ብሔራዊ የሽግግር እቅድ ግብርናውን ቁልፍ መሳሪያ በማድረግ አካታች የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት እንሰራለን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ሶማሊያ ቀጣይነቱ የተረጋገጠ የግብርና ስርዓት ለመዘርጋት፣ የማይበገር የምግብ ስርዓት እውን ለማድረግና የአየር ጸባይ ለውጥን ለመከላከል በቁርጠኝነት እየሰራች እንደምትገኝም ነው ያረጋገጡት፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!