የአረርቲ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የሴራሚክ ምርት ለገበያ አቀረበ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአረርቲ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ከ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የሴራሚክ ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ አቅርቧል።
የፓርኩ ስራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ ቦሰት ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በፓርኩ የሴራሚክ፣ ጨርቃ ጨርቅና ችፑድ አምራች ፋብሪካዎች በመሰማራት ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛል።
በተለይም ፓርኩ የሴራሚክ ምርትን በብዛት በማምረትና ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ከውጭ የሚገባውን ምርት በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህም በበጀት ዓመቱ 3 ሚሊየን 172 ሺህ 546 ሜትር ኪዩብ ሴራሚክ በማምረት 2 ቢሊየን 942 ሚሊየን 890 ሺህ 816 ብር በሀገር ውስጥ ገበያ መሸጥ መቻሉን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ ኢንዱስትሪ ፓርኩ በሦስቱ ፋብሪካዎች ያመረታቸውን ምርቶች 3 ቢሊየን 153 ሚሊየን 617 ሺህ 626 ብር በመሸጥ ገቢ ማግኘቱን ጠቁመዋል።
ፓርኩ በሴራሚክ ምርት ብቻ ለአካባቢው ማህበረሰብ የገበያ ትስስር በመፍጠር ረገድ 589 ሚሊየን 58 ሺህ 586 ብር የተለያዩ ቁሳቁስ በመግዛት ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻሉን ገልጸዋል።
በፋብሪካዎቹ ለ1 ሺህ 345 ሰዎች የስራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸው÷ ለሰራተኞቹ የተለያዩ ሙያዊና ደኅንነታቸው መጠበቅ የሚያስችሉ ስልጠናዎች በየጊዜው እንደሚሰጣቸውም አመልክተዋል።
ኢንዱስትሪ ፓርኩ ሥራ ከጀመረ ጀምሮ ባመረታቸው ተኪ ምርቶች 57 ሚሊየን 375 ሺህ 637 የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማዳን መቻሉንም አቶ ታደሰ አስረድተዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!