Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ ለማሳካት ዕቅዶቻችንን በትኩረት መፈፀም ይገባል- አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ ለማሳካት ዕቅዶቻችንን በትኩረት መፈፀም ይገባል አሉ፡፡

አጉባኤው እንዳሉት፤ በቀጣዩ ዓመት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ከፍታ ለማሳካት እንደ ሀገር በታቀዱት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ግቦች ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራት ይገባል፡፡

መልካም አጋጣሚዎች ላይ በመመስረት እና ተግዳሮቶችን ወደ በጎ ተፅዕኖ በመለወጥ በጥንካሬ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የ2018 በጀት ዓመት 6ኛ የፓርላማ ዘመን የስራ ጊዜ የሚጠናቀቅበት እና ሕዝብ የሰጠንን ሥልጣንና ኃላፊነት በተገቢው መንገድ ተጠቅመን ዕቅዶቻችን መፈጸማቸውን የምንመዝንበት ዓመት ነው በማለት አብራርተዋል፡፡

ድክመቶችን በማረም ለ7ኛው የፓርላማ ዘመን በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በፖለቲካ ዘርፍ ምቹ መደላድል የሚዘረጋበት ዓመት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በቀጣዩ ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ በወሳኝ አጀንዳዎች ላይ ምክክር የሚደረግበትና መግባባት ላይ የሚደረስበት ዓመት ነው ብለዋል፡፡

ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን እና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታችን መሠረት በመሆኑ ምክር ቤቱ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ በትኩረት መደገፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት የሕዝቦችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የተከናወነበት እንደነበር አስታውሰዋል።

ምክር ቤቱ በሕገ መንግሥቱ የተጣለበትን ሥልጣንና ኃላፊነት በብቃት መወጣት መቻሉ ለተያዘው በጀት ዓመት ጠንካራ መሠረት እንደሚሆነው ጠቅሰዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት ሪፖርትና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን አፈ ጉባኤ አቶ አገኘው የሥራ መመሪያ እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡

የጽ/ቤቱ አመራሮች እና ፈጻሚዎች በቀጣይ በጥናት ላይ የተመሠረተ ሙያዊ አገልግሎት መስጠት እንደሚኖርባቸው ማሳሰባቸውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ተረፈ በዳዳ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.