Fana: At a Speed of Life!

የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ በሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ ጉባዔ “ለአፍሪካውያንና ዘርዓ አፍሪካውያን የማካካሻ ፍትህን ለመሻት አህጉር ተሻጋሪ አጋርነት” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ጉባዔው የአፍሪካና ካሪቢያን ሀገራት በደቡብ ደቡብ የትብብር መንፈስ ግንኙነታቸውን ለማጎልበት፣ አፍሪካ ከካረቢያን ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እና ትብብር ለማሳደግ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ጉባዔው በዓለም የፋይናንስ ስርዓት፣ በቱሪዝም፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ይመክራል።

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.