Fana: At a Speed of Life!

 የአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ ግቦችን ለማሳካት ከተባበሩት መንግስታት ጋር መስራቱን ይቀጥላል 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ የአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ ግቦቹን ለማሳካት ከተባበሩት መንግስታት በትብብር መስራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል አሉ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ባካሄደው 79ኛ ጉባኤ ላይ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በትብብር ለመስራት ያሳለፈውን ውሳኔ አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት ሊቀመንበሩ፤ የተባበሩት መንግስታት ከአፍሪካ ህብረት ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያሳለፈውን ውሳኔ ህብረቱ በደስታ ይቀበለዋል ብለዋል።

ውሳኔው በአፍሪካ ህብረት እና በተባበሩት መንግስታት መካከል ሰላምና እና ደህንነትን እንዲሁም ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት በትብብር ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ከተባበርን ከአፍሪካ አልፎ ለዓለም መረጋጋት አስተዋፅኦ ማድረግ እንችላለን ያሉት ማህሙድ አሊ ዩሱፍ÷ የአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ ግቦቹን ለማሳካት በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በተለይም አጀንዳ 2063 እና የ2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ከተባበሩት መንግስታት ጋር በቅንጅት ለመስራት ህብረቱ ያልተቆጠበ ጥረት ያደርጋል ነው ያሉት።

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.