በመዲናዋ 10 የሂሳብ ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ እንዲሰረዝ ጥያቄ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የቅድመ ኦዲት ተግባር በማከናወን የመንግስትን ጥቅም በከፍተኛ ደረጃ ለመጉዳት የሚያስችል የገቢ ልዩነት የተገኘባቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ፈቃድ እንዲሰረዝ ጥያቄ አቅርቧል፡፡
ቢሮው ጥያቄውን በዛሬው ዕለት ለኢትዮጵያ የሂሳብ እና ኦዲት ቦርድ ያቀረበው በታክስ አስተደደር አዋጅ 983/2008 አንቀፅ 48 ንዑስ አንቀፅ 2 (ሀ) መሰረት ነው፡፡
በቢሮው የሙያ ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ጥያቄ የቀረበባቸው 10 የሂሳብ ባለሙያዎች እና ኦዲተሮች በቦርዱ የሙያ ፈቃድ የተሰጣቸው እንደሆነም ተገልጿል።
ቢሮው ከሂሳብ ባለሙያዎች እና ኦዲተሮች የሂሳብ መዝገብ አዘገጃጀት ላይ በሚስተዋሉ ግድፈቶች ላይ ከቦርዱና ከሙያ ማህበራት ጋር በተደጋጋሚ ውይይቶችን ስለማድረጉ ነው የተገለጸው፡፡
የሂሳብ ባለሙያዎች እና ኦዲተሮች ለቢሮው የሚያዘጋጁት የሂሳብ መዝገብ ማሟላት የሚገባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ በመፅሔት በማዘጋጀት ለሁሉም አካል እንዲሰራጭ መደረጉም ተገልጿል።
ቢሮው የሙያ ፈቃዳቻው እንዲሰረዝ ጥያቄ ያቀረበባቸው የሂሳብ ባለሙያዎች እና ኦዲተሮች በ2017 በጀት ዓመት ለግብር ከፋዮች ሂሳብ መዝገብ አዘጋጅተው በቅድመ ኦዲት ከፍተኛ ግድፈት የተገኘባቸውና በታክስ ስወራ የመንግስትን ጥቅም ሊያሳጡ የነበሩ ናቸው ተብሏል።
የከተማ አስተዳደሩ ግብር ከፋዮች ቢሮው የሙያ ፈቃድ ስረዛ በተጠየቀባቸው የሂሳብ ባለሙያዎች እና ኦዲተሮች ተዘጋጅተው የሚቀርቡ መዝገቦችን እንደማይቀበል አስታውቋል።
የሙያ ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ጥያቄ የቀረበባቸውን የሂሳብ ባለሙያዎች እና ኦዲተሮች ዝርዝር ከቦርዱ በመጠየቅ የሙያ ስነ ምግባሩን ጠብቀው በሚሰሩ የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች የሂሳብ መዝገቡን በማሰራት እንዲያቀርብ አሳስቧል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!