Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል በዓል በድምቀት እንዲከበር አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል በዓል እሴቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር ከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ነው አሉ።
ከንቲባዋ የመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅት እና የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመስቀል በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ የበዓሉ ዋና ባለቤትና በዓሉን የምትመራው፤ የምታስተባብረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብትሆንም በዓሉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በአደባባይ የሚያከብረው የሀገር ሀብት ነው ብለዋል።
የመስቀል በዓል የከተማችን ድምቀት፣ የቱሪዝም መስህብ ነው በማለት ገልጸው፤ ሃይማኖታዊ ትውፊቱን እና አብሮትን በሚያጠናክር መልኩ በድምቀት እንዲከበር የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ለመስቀል በዓል ብቻ ሳይሆን ሌሎች የአደባባይ ክብረ በዓላት ሲከበሩ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ አባቶች እና የኮሚቴው አባላት የመስቀል ደመራ በዓል መስቀል አደባባይን ጨምሮ በ2 ሺህ 375 ደብሮችና ቦታዎች ላይ እንደሚከበር ጠቅሰው፤ ለከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.