ጥቅምት የሳይበር ደህንነት ወር …
👉 የሳይበር ደህንነት ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ6ኛ ጊዜ ይከበራል፤
👉 ወሩ “የሳይበር ደህንነት – የዲጂታል ኢትዮጵያ መሰረት” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ይከበራል፤
👉 የተቋማትን እና የኅብረተሰቡን የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና ማጎልበት ላይ ትኩረት ይደረጋል፤
👉 ሰዎች እና ተቋማት ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል እንዲችሉ የሚያግዙ መርሐ ግብሮች ይካሄዳሉ፤
👉 ሐሰተኛ መረጃ ዝግጅትና ስርጭት መከላከል፣ ዲጂታላይዜሽን እና የሳይበር ደህንነት የወሩ ዋና ዋና ጭብጦች ናቸው፤
👉 የተለያዩ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል፤
👉 ዜጎችን የሚያሳትፉ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊናን የሚያጎለብቱ የተለያዩ ውድድሮች ይካሄዳሉ፤
👉 የሕብረተሰቡንና የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና የሚያጎለብቱ የሚዲያ ንቅናቄ ሥራ ይሰራል፤
👉 በዩኒቨርሲቲዎችና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሳይበር ደህንነት ክበባትን የሚያበረታቱ ሥራዎች ይሰራሉ።