Fana: At a Speed of Life!

ክልሉ 7 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል የቅባት እህል ለውጪ ገበያ ለማቅረብ አቅዷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል በ2018 በጀት ዓመት 7 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል የቅባት እህል ለውጪ ገበያ ለማቅረብ ታቅዷል።

የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በጥራጥሬና የቅባት እህል ዘርፍ የውጭ ንግድን ለማሳደግ ዓላማ ያደረግ የምክክር መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጎንደር ከተማ እያካሄደ ነው።

የቢሮው ኃላፊ ኢብራሂም ሙሀመድ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት፤ ለሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች እና ለውጪ ገበያ የሚቀርበው የቅባትና የጥራጥሬ ምርት መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 6 ነጥብ 9 ሚሊየን ኩንታል የቅባት ምርት ለውጭ ገበያ መቅረቡን ገልጸው፤ በ2016 በጀት ዓመት ከተላከው ምርት የ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል ብልጫ እንደነበረው አስታውሰዋል።

ከግብይት ጋር በተያያዘ የሚታየውን ሕገ ወጥነት ለመቀነስ አሰራሮች መዘርጋታቸውን አንስተው፤ በዚህ ዓመት ግብይት ወቅት በክልሉ የተዘጋጀ የምርት መሸኛ ተግባራዊ እንደሚሆን አመልክተዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት 7 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል የቅባት እህል ወደ ውጭ ለመላክ መታቀዱን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል የቅባት እህል ምርት ለሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች ለማቅረብ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ህገወጥ የግብይት ሂደትን ለመከላከል ከፀጥታ ተቋማት ጋር እየተከናወነ ያለው የተቀናጀ ተግባር በዚህ ዓመት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኃላፊው አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የሰሜን ቀጠና አስተባባሪ መዝገቡ ክንዴ በበኩላቸው፤ ባለሀብቱ ከቅባት እህል ምርቶች ጋር በተገናኝ የሚያነሳውን ቅሬታ ለመፍታት አሰራሮች ተዘርግተዋል ብለዋል።

ከምርት እና ደረጃ አሰጣጥ ጋር የሚቀርቡ ጥያቄዎች በፍጥነት እንዲመለሱ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በምናለ አየነው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.